በበእምነት መካከለኛ ክሊኒክ፣ ትልቁ ስኬታችን የታካሚዎቻችን ጤና መሻሻል ብቻ ሳይሆን፣ ለምንኖርበትና ለምናገለግለው ማህበረሰብ የምናበረክተው አስተዋጽዖ ነው። ክሊኒካችን የተመሰረተው ለቤሌ አዋሳ ህዝብ ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ብቻ ሳይሆን፣ ከህዝባችን ጎን በመቆም አብሮ ለማደግ ነው።
እኛ እንደ አንድ የጤና ተቋም፣ ጤና የሚጀምረው ደህንነቱ ከተጠበቀ ቤት እና ጠንካራ ማህበራዊ ትስስር እንደሆነ እናምናለን። ለዚህም ነው በተግባር የሚከተሉትን ተግባራት ስናከናውን የቆየነው፡-
በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት፡ በመንግስት ጥሪ መሰረት አቅመ ደካማ ለሆኑ ወገኖች የመኖሪያ ቤት ግንባታ ላይ በንቃት ተሳትፈናል።
የማህበራዊ ጤና መድህን፡ የከተማዋ አስተዳደር ባቀረበልን ጥያቄ መሰረት፣ አቅም የሌላቸው ሁለት ወገኖች የዓመቱን የጤና መድህን ክፍያ በመሸፈን የህክምና ዋስትና እንዲያገኙ አድርገናል።
ለሰላምና ለስፖርት፡ የከተማዋን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ለሚገነባው የህዝብ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ግንባታ እንዲሁም ለወጣቶች ስፖርት ክለቦች የገንዘብ ድጋፍ አድርገናል።
ታማኝ ግብር ከፋይነት፡ ለአገራችን ዕድገት ያለብንን ግዴታ በመወጣት ግብራችንን በታማኝነት እንከፍላለን።
በእምነት መካከለኛ ክሊኒክ ሁልጊዜም ከንግድ ባለፈ ለቤሌ አዋሳ ህዝብ ደህንነትና ልማት በታማኝነት የሚቆም የህዝብ ተቋም ሆኖ ይቀጥላል።
በእኛ ላይ ላላችሁ እምነት እናመሰግናለን!
ጀንኑ ጌቱ እና ታዲዎስ ኡታሎ የበእምነት መካከለኛ ክሊኒክ ባለቤቶችና መስራቾች
At Bemnet Medium Clinic, we believe our responsibility extends beyond the walls of our clinic. We are proud to be active members of the Bele Awasa community, contributing to the growth, safety, and well-being of our neighbors in Wolaita Zone.
We believe that health starts with a safe home and a secure environment.
Summer Voluntary Service: In alignment with the government’s national initiative, our team actively participated in building homes for economically disadvantaged members of our community.
Community Safety: We provided financial contributions for the construction of the Bele Awasa Community Police Office to help ensure the safety and security of all residents.
We are committed to ensuring that no one is left behind when it comes to medical security.
Social Health Insurance (CBHI): This year, in collaboration with the Town Administration, Bemnet Medium Clinic covered the full annual social health insurance premiums for two families in need. This ensures they have access to the broader health system without financial burden.
A healthy community is an active community.
Empowering Local Youth: We provide ongoing financial sponsorship to various youth sports clubs in town. By supporting local sports, we help foster teamwork, discipline, and physical health among the younger generation in Bele.
Honest Taxpayer: Bemnet Medium Clinic is proud to contribute to the national economy of Ethiopia. We maintain a transparent and honest record of tax payments, ensuring that our success contributes directly to the public services and infrastructure of our country.